Blog Archives

በዶ/ር አረጋዊ በርሀ የሚመራ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ልኡክ አዲስ አበባ ገባ

በዶ/ር አረጋዊ በርሀ የሚመራ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ልኡክ አዲስ አበባ ገባ በ ዶክተር አረጋዊ በርሀ የሚመራ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ልኡክ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብቷል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሀን ጨምሮ ሌሎት የፓርቲው አባላት አዲስ አበባ የገቡት መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። ከፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሀ ጋርም አቶ መኮንን ዘለለው እና አቶ ግደይ ዘርአጽዮን አዲስ አበባ ገብተዋል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ልኡካን አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለልኡኩ አቀባበል ያደረጉት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፥ አሁንም በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መንግስት ጥሪውን ያቀርበባል ብለዋል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሀም፥ ጠቅላይ ሚኒስትድ ዶክተር አብይ ያቀረቡን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር መግባታቸውን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስት የጀመራቸውን ስራዎች እንደሚደግፉም አስታውቀዋል። ምንጭ ፦FBC
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News