Blog Archives

በደንቢዶሎ በምጥ የተያዘችውን የገደሉት ለፍርድ አልቀረቡም።

በምጥ የተያዘችውን የገደሉት ለፍርድ አልቀረቡም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ‘በምጥ ለተያዘች ነፍስ ጥይት?!’ በሚል ርዕስ በዚሁ ማሕበራዊ ገጽ ያጋራሁዋችሁ መረጃ ነበር። ጉዳዩ በአጭሩ በተጠቀሰው ዕለት ምጥ የጠናባት ወ/ሮ ብርሃኔ ማሞ ከሜጢ ከተማ ወደደምቢ ዶሎ ሆስፒታል ሪፈር ተብላ ደምቢዶሎ ከተማ ከምሽቱ 5:30 ላይ ስትደርስ በክልሉ ፖሊስ ልዩ ሃይል በጥይት ተገድላለች። አብረዋት የነበሩ የቤተሰቦቿ አባላት የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ ግፍ ጋር በተያያዘ በቀጣዩ ቀን ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ በከተማዋ ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን በግድያው ተሳትፈዋል የተባሉ ሶስት የፖሊስ አባላት ማለትም 1ኛ ኮንስታብል አብርሃም ስዩም፣ 2ኛ ኮንስታብል በቀለ በዳዳ(Badhaadhaa)፣ 3ኛ ኮንስታብል መልካሙ ነጋሳ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንደተጀመረ ጠቁሜ ነበር። እውነታው ግን ከዚያ የተለየና አስደንጋጭ የማናለብኝ የፍትሕ ጥሰት እየተፈፀመ መሆኑን ዛሬ ያነበብኩት የረዥም እስር አጋሬና ጓደኛዬ የ Lammii Beenyaa መረጃ አረጋግጦልኛል። ተጠርጣሪዎቹ እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረቡም! ያሳዝናል፤ ልብ ይሰብራል! በደምቢዶሎ ከሚገኙ ጓደኞቼ ደውዬ እንዳረጋገጥኩትም ሁኔታው ሆን ተብሎ ሕዝቡን ወደቁጣ ለመምራት በሚመስል መንገድ የፍትሕ መበየንን ወደጎን በማድረግ ጉዳዩን ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ በመስጠት ለመሸፋፈን እየተሞከረ ነው ብለውኛል። በቁጥጥር ስር ዋሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ያሉበት ወታደራዊ ካምፕም በቀላሉ ለማምለጥ አመቺ መሆኑ ሕዝቡን ቁጭት ውስጥ እንደከተተው ነግረውኛል። በምጥ ስትቃትት በጥይት ናዳ ያለፈችው የወ/ሮ ብርሃኔ ደምና ይህችን ምድር እንዳይቀላቀል በግፍ የተቀጨው ህፃን ነፍስ ይጮሃሉ። ይህን ግፍ አቅልሎ ማለፍ የህሊናም፣ የመንፈስም፣ የነፍስም፣ በአጠቃላይም የሰው መሆን ዕዳችን ነው። ደጋግመን እንላለን፤
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደምቢዶሎ በምጥ የተያዘችዋን እርጉዝ ሴት የገደሉት የኦሮሚል ልዩ ፖሊሶች መሆናቸው ታውቋል።

የዘግናኙ ወንጀል ፈጻሚዎች እነማናቸው? በትናንትናው ዕለት እኩለ ሌሊት አከባቢ በምጥ ጣር ተይዛ ወደ ደምቢዶሎ ሆስፒታል በመሄድ ላይ በነበረችው የ35 ዓመት ወጣት ላይ ስለተፈጸመው ዘግናኝ ግድያ ያጋራሁዋችሁ መረጃ ነበር። ቀጥሎ ያለውን ተጨማሪ መረጃ(follow up) ያገኘሁት የእስር አጋሬ ከነበረው ‘Lammi Beenyaa’ ገጽ ላይ ሲሆን መልዕክቱንና መረጃውን ከአፋን ኦሮሞ ወደ አማርኛ አጠር አድርጌ በመመለስ ላካፍላችሁ። ወ/ሮ ብርሃኔ ማሞ ከደምቢዶሎ አምስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሜጢ የህክምና ጣቢያ ከደረሰች በሁዋላ ከምጧ ከባድነት የተነሳ በጣብያው ልትረዳ ስላልቻለች ሪፈር የተባለች ሲሆን፤ ሲስተር ሲቲና የተባለችው የህክምና ባለሙያ ሪፈር ከመጻፏ በፊት ለከተማው የአምቡላንስ ሹፌር ብትደውልም አሽከርካሪው ፈቃደኛ ሳይሆን ይቀራል። ለሰዮ ወረዳ የጤና ቢሮ ሃላፊ ለአቶ ጫላ ዋቅጅራና ለምክትላቸው ቢደወልም ሁለቱም ስልካቸውን አይመልሱም። ከዚህ በሁዋላ አማራጭ ያጡት የነፍሰ ጡሯ ቤተሰቦች ባጃጅ ተከራይተው ጉዞ ወደ ደምቢዶሎ ሆነ። – በሕዝብ ገንዘብ የተገዛ አምቡላንስ ለዚህ የችግር ቀን ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ነው? አምቡላንስ እንዳይንቀሳቀስ የከለከለውስ ማነው? ይህች ባጃጅ ደምቢዶሎ ከተማ ስትገባ በኦሮሚያ ፖሊስ ልዩ ሃይል ተኩስ እንደተከፈተባት የቄለም ወለጋ የጸጥታና ደህንነት ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ ጸጋዬ ዋቅጅራ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ አረጋግጠዋል። ለክስተቱ መንስኤ የነበረውም የከተማዋ የሰዓት ዕላፊ እስካሁን ያለመነሳቱ መሆኑንና ድርጊቱን ሳያጣሩ የፈጸሙት ፖሊሶች ሁኔታውን ካወቁ በሁዋላ በመደናገጥ ተጎጂዎቹን ወደሆስፒታል እንዲወሰዱ ቢያደርጉም እጅግ ዘግይተው ነበር። በተኩሱ በምጥ ጣር ላይ የነበረችው ወ/ሮ ብርሃኔ ህይወቷን ስታጣ ድጋፍ ሲያደርጉላት የነበሩት የቤተሰቧ አባላት የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ደርሶባቸዋል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News