Blog Archives

ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እንዴት? ( ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር))

ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እንዴት? *** ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር) *** ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት (multinational) አገር ብትሆንም፣ ይህንን ኅብረ ብሔራዊነቷን የሚያስተናገድ ሥርዓት መገንባት አልቻለችም፡፡ በአገራችን ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እስካልተገነባ ድረስ ግን ዕድገት ብሎ ነገር የሚታሰብ አይሆንም፤ ይልቁንም ግጭቱና የሕዝብ መፈናቀሉ ሥር እየሰደደ ይቀጥላል፡፡ ሄዶ ሄዶም የዘር ፍጀት የሚከሰትበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ይህ እንዳይሆን፣ ሳይረፍድ ከአሁኑ መላ ልንፈልግ ይገባናል፡፡ የኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት መሠረቱ ዴሞክራሲ ነው፡፡ ያለ ዴሞክራሲ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓትን ማሰብ አይቻልም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት ከፀደቀ ወዲህ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት ወይም በተለመደው አማርኛ “ዴሞክራሲያዊ አንድነት” ተገንብቷል ይላሉ፡፡ ይህ አስተያየት ግን ፈጽሞ ውኃ የሚቋጥር አይደለም፡፡ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት ያለ ዴሞክራሲ አይታሰብም፡፡ ኢትዮጵያም ደግሞ ዴሞክራሲያዊት አገር አይደለችም፡፡ ስለሆነም በአገራችን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ብሎ ነገር የለም፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያለው ፌደራላዊ ሥርዓት ብዙ ጠቃሚ ጎኖች ቢኖሩትም ያሉበት እንከኖችም በጣም በርካታ ናቸው፡፡ አንደኛውና መሠረታዊው ችግሩ፣ በብሔረሰቦች መሀከል ያለው መስተጋብር በጎና ሰላማዊ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ፣ እያንዳንዱ ብሔረሰብ የራሴ የሚለውን ክልል ወይም ዞን ወይም ልዩ ወረዳ “የእኔ ብቻ ነው፤ ማንም ሊደርስብኝ አይችልም፤ አይገባምም፤” ብሎ “ሌሎችን” ማኅብረሰቦች ከአካባቢው ሲያባርር፣ የሥራ ዕድል ሲከለክልና ሲገድል ነው የሚታየው፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ማንኛውም ዜጋ፣ በራሱ ቋንቋ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ ተዘዋውሮ የመሥራትና የመኖር መብቱን የሚያስከብርበት፣ ይህ መብቱ ሳያከበር የቀረ እንደሆነ ወደ ፍርድ ቤት አቤት ብሎ መብቱን የሚያስከብርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስላልተመሠረተ ነው፡፡ የዜግነት መብትን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News