Blog Archives

ባሕር ዳር ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ከተደረጉ ንግግሮች በከፊል

ዛሬ ሀገራችን ደስታና ፍቅር ብቻ የሚታይባት ሀገር አይደለችም:የኛ አንድ መሆን የእግር እሳት የሆነባቸው ያልታደሰውና አሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ከግር እግራችን ስር እየተከታተሉ መንገዳችንን በስጋት ድል ሊያሰናክሉ ሲሞክሩ እየታዩ ነው::ሰላም የዋለው ሀገር ሰላም እንዳያድር:ለሰላም የተዘረጉ እጆች ሳይጨባበጡ እንድቆራረጡ ስራ ውለቴ ብለው የሚደክሙ:ሽንፈትን ያልተቀበሉ ደካሞች ከዙሪያችን አልጠፉም:: ( አቶ ገዱ አንዳርጋቸው! ) አቶ ደመቀ መኮንን በባህር ዳሩ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ መልዕክቶች፡- • ‹‹ይህ ትዕይንት ሃይልም፤ ጉልበትም ነው!›› • ‹‹ይህ አስደማሚ አንድነት የድህነትን አለት ሲሰባብር ይታየኛል!›› • ‹‹አንጀታችን እንደክራር፣ ልባችንን እንደከበሮ በጋራ የሚደልቅበት አንድነት ፈጥረናል!›› • ‹‹የድጋፍ ሠልፉ የአደራ ጥራዝ የብርታት ለውጥ ነው!፤ አደራዉ የጋራ ነው ለውጡም የሁላችን ነው፤ አደራውን ሰምተን፣ ለውጡን ተቀብለን ለመስራት ዝግጁ ነን፡፡›› • ‹‹በቀደሙት አባቶች የታፈረችውን ሀገር በእኛ ዘመን በርትተን አናሳድጋለን!›› • ‹‹ምሁራንም ብዕራችሁ የተባ፣ አዕምሯችሁ የሰላ ሊሆን ይገባል!›› • ‹‹ያለፉትን ስርዓቶች እየረገምንና እየወቀስን እዚህ ደርሰናል፤ከዚህ በኋላ ግን ስራችንን በዲሞክራሲ መንገድ ልትታገሉት ይገባል!›› የሽግግር መንግስት ልናቋቁም ነው ወይስ በተቀደደልን ቦይ ልንፈስ ነው?  (እማዋይሽ አለሙ) “ይህን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ጥቅማቸው የሚነካባቸው ካሉ አብረን እንታገላቸዋለን” ( ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ) አንድ ስንሆን የማይደፈሩ መስለው ይታዩ የነበሩ ተራሮችን መናድ እንደምንችል ተምረናል:: (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው) “መጪው ጊዜ የአማራ ህዝብ የሚሰደብበትና የሚሸማቀቅበት ሳይሆን ቀና ብሎ የሚሄድበት ነው” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው   ሙሴ እስራኤልን ነፃ አወጣ ኢትዩጵያን አብይ ነፃ አወጣ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በባህር ዳር ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ በመካሔድ ላይ ይገኛል።

በባህር ዳር ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ በመካሔድ ላይ ይገኛል። አማራ መነሻ እንጂ መድረሻ አልቀየረም ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያዊነት ነው።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News