Blog Archives

ከመተሃራ አልጌ የሚባል ቦታ 40 አማራዎች በአከባቢው አመራሮች አነሳሽነት ተፈናቅለዋል።

ሌላ የአማራ መፈናቀል ዜና! የካቲት 8/2010 ዓም ከመተሃራ አልጌ የሚባል ቦታ 40 ያህል አማሮች በአከባቢው አመራሮች አነሳሽነት ተፈናቅለዋል። በአሁኑ ወቅት 15 የፈናቃዮች ደጀን ከተማ ይገኛሉ። 17 አባውራዎች ወደወሎ ሄደዋል ተብሏል። ደጀን የሚገኙት:_ 1) መለሰ ሀይሌ፣ ሁለት ልጆች፣ ባለቤቴ ጋር በኦህዴድ አመራሮች ተባርሯል። ባለቤቱ ባንቺአይሞሉ ምናለው እና ልጃቸው ተመስገን መለስ(የ8አመት)፣ ፍቅርተ መለሰ(3 አመት) ሲሆኑ ሁለቱም ልጆቻቸው ሕመም ላይ ናቸው። 2) ካሳ ወንድይራድ ከሁለት ልጆቿ ጋር ኦህዴድ አፈናቅሏታል። ታደሰ ይፈርድ(16 አመት) እንዲሁም ረድኤት ይፍረድ (9 አመት) ልጆች ናቸው። 3) ትብለጥ አድማሱ ከሁለት ልጆቿ ጋር ተፈናቅላለች። በረከት አምጤ (12 አመት)፣ በሱፉቃድ አምጤ (3 አመት) ልጆች ናቸው። 4) ተስፋዬ እጅጉ ከባለቤታቸው ደመቁ ጤናውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል። አቶ ተስፋዬ አንድ እጅ ጉዳይ ያለባቸው ሲሆን የ5 አመት እና የ6 ወር ልጆች አሏቸው። 5) እየሩስ ከ4 አመት ልጇ ጋር ተፈናቅላለች 6) አለሙ አበራ የሚባል ሰው በወቅቱ እንደተገደለና ብዙዎቹ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልፆአል። አመራሮቹ “አማራን አስወጡት” ብለው አዝዘው እንዳፈናቀሏቸው ተፈናቃዮቹ በስልክ ገልፀውልኛል። ደጀን ከተማ የሚገኙትን 15 ተፈናቃዮችን ግለሰቦች ብቻ የተወሰነ ድጋፍ እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ በችግር ላይ እንደሚገኙም ተገልፆአል።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይም ፕረዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ አስደናቂ ውሳኔ ማሳለፉን OBN ዘገበ።አማራዎችን ከኦሮሚያ ክልል ያፈናቀሉ ባለስልጣናት መባረራቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ድርጅት ጠቁሟል። በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅላችኋል፣ ወይም ለማፈናቀል ሞክራችኋል፣ ጥላቻን ዘርታችኋል፣ ወይም ህዝብ ለህዝብ እንዲጣላ ምክንያት ሆናችኋል የተባሉ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ ና የልዩ ልዩ ቀበሌዎች አመራሮችን አሰናብተዋል፣ የአንዳንዶቹም በህግ እንዲታይ አድርገዋል ብሏል የክልሉ ቴሌቪዥን። <<..የአማራ ህዝቦች ወንድሞቻችን ናቸው፣ ያለ እነሱ እነሱም ያለኛ..ወይም አንዳችን ያለ አንዳችን መኖር አንችልም..በቅርቡ የመጣውን ለውጥ እንኳን ተመልከቱ፣ የሁሉቱ ክልል ህዝቦች ትግል ነው..አሁን የምታዩት ለውጥ ያመጣው… የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እየኖሩ ነው፣ ስለሆነም ወንድሞቻችን በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ስጋት ሰርተው እራሳቸውን መለወጥ፣ ሀብት ማከማቸት ይችላሉ፣ አንዳንዶች በኦሮሚያ ና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ አለመተማመንን ለመፍጠር እየተሯሯጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት የታየ ድርጊት መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ስለዚህ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ይንን ሴራ መመከት ያስፈልጋል.. >>..ሲሉ ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትም ተናግረዋል ሲል ነው የዘገበው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News