Blog Archives

“ወደ ሀገራችሁ ሂዱ” :- ሃይ ባይ ያጣው የአማሮች መፈናቀል! (ቪድዮ)

ሃይ ባይ ያጣው ብሔር ተኮር መፈናቀል! “ወደ ሀገራችሁ ሂዱ” :- በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙና ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ዘላቂ መፍትሄ እንሻለን ይላሉ። በራያና ቆቦ፣ ጉባ ላፍቶ እንዲሁም ሀብሩ አካባቢዎች በከተሞች እና በገጠር ቀበሌዎች የተሰባሰቡት ተፈናቃዮች በመቶዎቹ የሚቆጠሩ እንደሆነ ሲዘገብ ቢቆይም፤ ከትናንት በስትያ የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅት አንድ ሺህ አራት መቶ እንደሚጠጉ አትቷል። ቁጥሩ ከዚህም እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ቢቢሲ ያናገራቸው ተፈናቃዮች ይገልፃሉ። የ42 ዓመቱ አቶ ተበጀ ጉበና ገና የስድስት ወይንም የሰባት ዓመት ልጅ ሳሉ በወቅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ተከሰቶ የነበረውን ድርቅ እና ረሃብ ተከትሎ በወቅቱ መንግሥት የሰፈራ መርኃ ግብር አማካይነት ከደምቢ ዶሎ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ገላን መቲ የገጠር ቀበሌ መኖር እንደጀመሩ ይገልፃሉ። ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት የመንግሥት ለውጥ በነበረበት ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ያህል ወደ ትውልድ ቀያቸው ራያ ቆቦ ከመመለሳቸው በስተቀር ህይወታቸውን በሙሉ በዚያው ሲመሩ እንደቆዩ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን የ”ውጡልን” ድምፆችን መበርታትን ተከትሎ በስጋት ሲናጡ መክረማቸውንም ያስረዳሉ። ስጋቱን ተግ የሚያደርግ ነገር አላገኘሁም የሚሉት አቶ ተበጀ የግብርና ሥራቸውን ትተው ወደቆቦ ከተማ ያመሩት ከስድስት ወራት በፊት እንደሆነ ይናገራሉ። “ታላቅ እና ታናሽ ወንድሞቼ ግን በዚህ ሦስት ሳምንት ውስጥ ነው የመጡት። አባቴ እና የእህቴ ባል እዚያው ናቸው። ለመምጣት እየተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “እህቴም በእርግጥ ልጆቿን ይዛ መጥታለች።” የራያ እና ቆቦ ወረዳ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ባለሞያ የሆኑት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው)

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው) በኦሮሚያ ክልል በብዙ ዞኖች አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌና ሌሎችም የአዲስ አበባ ዙሪያ ዞንን ጨምሮ አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ አንዱ ሲያቆም ሌላው እየተከተለ ሁሉም ቦታ ተፈናቃይ ብቻ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ የሚፈናቀሉት በሕወሓት ትእዛዝ ነው ማለት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም አማሮች እየተፈናቀሉ ያሉት ለአማራ ተወላጆች ከ2 ሔክታር መሬት በላይ አይገባቸውም በሚል ከኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በወረደ ትእዛዝ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባና እንግልት ያደርሳሉ፡፡ ለምን ብለው የሚጠይቁ በወንጀለኛነት ይታሠራሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው ከአመያና ኖኖ ወረዳ ቤት ንብረታቸው ወድሞ እንደገና 14 ዓመት በላይ እስር ተፈርዶባቸው በአምቦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አማሮች አሉ፡፡ የሚፈጠሩ አጋጣሚዎችን ሁሉ ወደብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚጥሩ አካላት በሁለቱም በኩል እንዳሉ እሙን ነው፡፡ ይህ ችግር የኦሮሞ ሕዝብ ችግር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ ችግሩ የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው፡፡ አቶ ለማና ዶክተር ዓቢይ ለአገር አንድነት እንሠራለን እንደሚሉት የዚህን ጉዳይ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጡት ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን የሚከተለውን ቀውስ ለመተንበይ የግድ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም በሰከነ አእምሮ የሚያስብ ማንኛውም ፍጡር ሁሉ ይህን ኢሰብአዊ ድርጊት እያወገዘ ውስብስብ ችግር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ልንጠይቅ ይገባል፡፡
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከ406 በላይ የራያ አማራዎች ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ያለ ታዛቢ በቆቦ ሜዳ ላይ ተበትነው ይገኛሉ ።

ስደትና መፈናቀል እጣ ፈንታው የሆነው አማራ በቆቦ! አማራነት ስዴት መከራና እንግልት ሆኗል ። አማራ እንኳን ከተኮለኮለለት ድንበር ውጭ በራሱም ባድማ ክብር ከተነፈገው ሁለት አስርተ አመታትን አስቆጥሯል ። ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉምዝ በክልሉ መንግስት መዋቅር ተሳታፊነት ጭምር ኃብት ንብረታቸው ተወርሶ በግፍ ከተባረሩት ምንዱባን ኃዘንና ቁጭት ሳናገግም ከ406 በላይ የራያ አማራዎች ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ያለ ታዛቢ ሜዳ ላይ ተበትነው ይገኛሉ ። ከእነዚህ ተፈናቃዮች ውስጥ በጣት የሚቆጠሩት ብቻ መጠነኛ የመንግስት ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን በርካታዎቹ በየቀበሌው ተበትነው አሳዛኝ ህይዎት እየገፉ እንደሚገኙ ተረድቻለሁ ። የወገኖቻችንን ግፍና እንግልትጰ በመመከት የጀመርነው የማንነት ጉዞ የነዚህን ወገኖቻችንንም እምባ ሊያብስ ፣ ጠኔ ሊፈውስ ፣ጥም ሊያረካና እርዛት ሊሸፍን ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ። አማራ ለራሱ ለአማራ ሞልቶ ሲተርፍ በቅርቡ። አስተውለናል። ወደፊትም ይበልጥ እናያለን። የተለመደው አኩሪ ትብብርና ድጋፋችን ፣ አለኝታነታችን ፣ ወገንተኝነታችን ለነዚህ ግፉዓን ሊደርሳቸው ይገባል ። ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ስለነዚህ ወገኖቻችን እንድንጮህ ፣ እጃችንን እንድንዘረጋና ለርሃብና ጥማታቸው ፈውስ እንድንሰንቅ ወንድማዊ ጥሪየን አቅርቤያለሁ። ጥሪየን በመቀበል፣ ጬኸቴን በማስተጋባት ኩራቶቼ እንደምትሆኑ በጽኑ አምናለሁ! Image may contain: 1 person የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች መፍትሄ አላገኘንም ይላሉ “ወደ ተፈናቀልንበት መመለስ ራስን ለሞት መስጠት ነው” (ቄስ ምናለ አያሌው፤ ተፈናቃይ) ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይ ዞን፣በለው ጅንጋፍወይ ወረዳ፣ ዴዴሳ ቀበሌ፣ ባለፈው ጥቅምት ወር በክልሉ ተወላጅ ወጣትና በአማራ ተወላጅ ወጣት መካከል በተፈጠረ ጠብ፣ የክልሉ ወጣት ህይወት ማለፉን ተከትሎ በተነሳ ግጭት 13 ሰው መሞታቸውን፣49 ከባድ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News