Blog Archives

በአፋር ክልል ሆስፒታሎች ሥራ እያቆሙ ነው

በአፋር ክልል ሆስፒታሎች ሥራ እያቆሙ ነው በአንዲት አገር ውስጥ ዜጎች ከመንግስት ማገኘት ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ የጤና አገልግሎት ማገኘት ነው፡፡ የአፋር ክልል ምንም እንኳን አጥጋቢ ባይሆንም ክልሉ ራሱ በራሱ የመስተዳድር እድል ካገኘ ወዲህ በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች ቁጥር 6 አድርሰዋል፡፡ እነዚህ ሆስፒታል በሥም እንጅ የተሟላ አገልግሎት ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ እያሰጡ ባለመሆኑ ዜጎች ለህክምና ፍላጋ ወደ ጎራቤት ክልሎች በመሄድ ለከፍተኛ ውጭ እየታረጉ ይገኛል፡፡ በተላይ በ2010 ላይ ክልሉ በጤና ዘርፍ ወደታች እያሽቆለቀለ ሆስፒታሎች ለሳምንት ምንም አይነት አገልግሎት ሳይሰጡ የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉበት ሁኔታ የታየበት ሁኔታም አለ፡፡ ለዚህ መንስኤው ደግሞ ከሁለት ወራት በላይ የሆስፓሉ ሠራተኞችና ሙያተኞች ወረሃዊ ደሙር አለመከፈልና ከ6 ወር ባለፈ ግዜ ለሐኪሞች የDuty ክፍያ አለመከፉሉ ነው፡፡ በመመድ አክሌ ሆስፒታል የተጀመረው የሥራ ማቆም ህደት እየሰፋ ዛሬ ደግሞ አብዓላ ሆስፒታል ላይ ቀጥለዋል፡፡ ወላድ እናቶች ሆስፒታሉች እየዘጉ ወደቤታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ ከየሆስፒታሉም የመፍትሔ ይሰጠን ጥያቄ ለምመለከተው አካል ቢቀርብም ውጤት አልባ ሆኗዋል፡፡ በስንት መከራ የተገኙ ሙያተኞች ሆስፒታሉን ለቀው ወደሌላ ክልሎች በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቂያ እያስገቡ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ? ወዴት ነው እያማራን ያለነው? ሆስቲታሉች በእንዲህ አይነት ችግር ውስጥ ከሆኑ ጤና ጣቢያ ጤና ኬላዎች እንዴትስ ሊሆኑ ይችላሉ ሆድ ይፍጀው  
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News