Blog Archives

ክቡር ኢትዮጵያዊነት አዛውንቱ አብራሪ ኮሎኔል ብርሃነመስቀል ኃይሌ

ክቡር ኢትዮጵያዊነት አዛውንቱ አብራሪ ኮሎኔል ብርሃነመስቀል ኃይሌ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የዘመናዊ የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ ። ኮሎኔሉ በበረራና ግዳጅ በመወጣት ብቃታቸው በጊዜው የአገሪቱን ከፍተኛ የጀግንነት ኒሻን አግኝተዋል።… የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ካፒቴን የነበሩት አዛውንቱ ብርሃነመስቀል ኃይሌ ኢህአዴግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ወህኒ ከወረወራቸው የአየር ኃይሉ ጅግኖች በራሪዎች መካከል አንደኛው ናቸው ። ለድፍን 20 ዓመታትም በእስር እንዲቆዩ ተደርገዋል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ስርዓቱ ለውጊያ ፈልጓቸው የተለያየ መደለያ ቢያቀርብም “ሻዕቢያ አገሬን ወርሮ ዝም አልልም። ግዳጄን ፈፅሜ ስመለስ ግን እናንተንም አለቃችሁም” በማለታቸው ለወራት ከሌሎች እስረኞች ተነጥለው እንዲታሰሩና በቤተሰብ እንዳይጎበኙ ተደርገውም ነበር። ጀግናው ኮ/ል ብርሃነመስቀል በእሁዱ ሰልፍ ላይ ተገኝተውም ድጋፋቸውን መግለፃቸውን ከምስሉ መረዳት ይቻላል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News