Blog Archives

ዶክተር አቢይ አሕመድ የአረፋና የኢድ አል አደሀ በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ አረፋና በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ የአረፋና የኢድ አል አደሀ በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የላከው የመልካም ምኞት መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። በሀገር ቤት እና ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ፤ በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ በክብር ለሚነሳው እና ዘንድሮም ለ1439ኛ ዓመተ-ሂጅራ ለሚከበረው የኢድአል አድሃ አረፋ በአል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ- አደረሰን! ኢድ ሙባረክ !!! በፆም፣ በፀሎትና ክፉ ምግባርን በሚኮንን ሀይማኖታዊ ሥርዓት የሚከናወነው የአረፋና የሀጅ ሥርዓት ከአምስቱ የእስልምና መሠረታዊ ምሶሶዎች መካከል አንዱ ሲሆን በእስልምና ሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ታለቅ በዓል ነው፡፡ በእምነቱ አስተምህሮት በግልጽ እንደተቀመጠው በዙል ሂጃህ ወር ዘጠነኛ ቀን የሚከናወነው የአረፋ ሥርዓት የእስልምና ሃይማኖት የመጨረሻ ከፍታውን ያገኘበት እና የቁርአን የመጨረሻ አንቀፆች ለነቢዩ መሀመድ (ሠዓወ) የወረደበት እለት ከመሆኑም በተጨማሪ በአንድ በኩል አደምና ሀዋ ከጀነት ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድር የተገናኙበትና አወቅኩሽ አወቅሽኝ የተባባሉበትን ድንቅ ተዓምራት ማስታወሻም ጭምር ነው፡፡ ነቢዩላ ኢብራሂም በፈጣሪያቸው ትዕዛዝ አንድ ልጃቸውን እስማኤልን ለመስዋዕት አቅርበው ለፈጣሪያቸው ትዕዛዝ ከመገዛታቸው የተነሳ በልጃቸው ምትክ የበግ መስዋዕትነት የተተካላቸው መሆኑን የምናስታውስበት ዕለት በመሆኑ ለሁላችንም የታዛዥነትን ከፍታ እና የእምነትን ልእልና የሚያጸድል ግሩም በአል ነው፡፡ ውድ የሀገራችን የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቼ !!! የዘንድሮውን የአረፋና ኢድ አልአድሃ በዓል ልዩ የሚያደርገው ሀገራችን
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News