Blog Archives

የአማራ ሕዝብ ማንን ይመርጣል? (ጌታቸው ሺፈራው)

የአማራ ሕዝብ ማንን ይመርጣል? (ጌታቸው ሺፈራው) ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ፣ ባለፉት 10 አመታት ወደመዘጋት ደርሶ የነበረው የፖለቲካ ምህዳር መስፋት ጀምሯል። ይህን መልካም አጋጣሚ ድርጅቶች ወደሕዝብ ለመግባት እየተጠቀሙበት ነው። አማራው ሕዝብ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ለማየት ብንሞክር እንኳ ብአዴን፣ አብንና አርበኞች ግንቦት ሰባት ከሌሎች በተሻለ ራሳቸውን ለማጠናከር ተፍ ተፍ እያሉ ይገኛሉ። 1) ብአዴን:_ ባለፉት 27 አመታት ሕዝብን ሲያስገዛ የኖረው ብአዴን የዶክተር አብይ አይመድን “መደመር”ና መሰል ፍልስፍናዎች ጠገግ አድርጎ፣ እነ ዶክተር አብይ አህመድ በሕዝብ ያገኙትን ተቀባይነት መሰረት በማድረግ በሕዝብ ልብ ለመግባት ተፍ ተፍ እያለ ነው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው ባህርዳር በተደረገው ሰልፍ ላይ “ከአሁን በኋላ አማራ አንገቱን አይደፋም” ብለዋል። እነ ተቀባ ተባባል ሀምሌ 5 የአማራ ሕዝብ የነፃነት ቀን ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የአማራ ተጋድሎን እውቅና መስጠት ጀምረዋል። ይህን የሚሉት የዶክተር አብይ አዲስ አስተሳሰብ ነው የሚሉትን ጠገግ በመያዝ ሲሆን ከሕዝብ የሚጠጉበት ብቸኛው አማራጭም “አዲሱ አስተሳሰብ” ነው እያሉ ነው። በዚህ ሂደት ትህነግ/ህወሓትና የቀድሞ የብአዴን አመራሮች ጋር ልዩነት እንዳላቸው በማስመሰል ለሕዝብ ራሳቸውን እንደአዲስ ማስተዋወቅ እየጣሩ ነው። የሕዝብ በደልና መከፋትን እውቅና እንደሚሰጡ ለማስመሰል እየጣሩ ነው። ብአዴን የአማራ ሕዝብ ላይ ተቀባይነት ባይኖረው እንኳ አደረጃጀቱን ይዟል። የዶክተር አብይን ተቀባይነት በኢህአዴግ ስር ሆኖ እየተጠቀመባት ይገኛል። ይሁንና ለ27 አመት የለመደበት የአስገዥነት፣ የአድርባይነትና የተላላኪነት አባዜ አልለቀቀውም። ከዚህም ባሻገር የአማራ ሕዝብ በኢኮኖሚው እንዲገለል፣ በሌሎች እንዲጠላ፣ ብዙ በደሎች እንዲደርሱበት የሰራ በመሆኑ በሕዝብ ዘንድ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News