Blog Archives

ክቡር ሚኒስትር አክቲቪስቶችና ፖለቲከኞች ሕዝብ በሚናገረው ቋንቋ፣ በሚለብሰው ልብስና በሚበላው ምግብ እየለያዩ የሚያጋድሉበት አገር ዜጋ ነኝ ለማለት አፍራለሁ፡፡

  ነገርኩዎት ክቡር ሚኒስትር አክቲቪስቶችና ፖለቲከኞች ሕዝብ በሚናገረው ቋንቋ፣ በሚለብሰው ልብስና በሚበላው ምግብ እየለያዩ የሚያጋድሉበት አገር ዜጋ ነኝ ለማለት አፍራለሁ፡፡ እ. . . ስለዚህ ኢትዮጵያ የሦስተኛ ዓለም አገር መሆን አይገባትም፡፡ እሱማ ካደጉት አገሮች ተርታ ለማሠለፍ ወጥረን እየሠራን ነው፡፡ ወዴት ወዴት ክቡር ሚኒስትር? ምነው? ኢትዮጵያ መመደብ ያለባት ሌላ ዓለም ውስጥ ነው፡፡ የትኛው ዓለም? አራተኛው ዓለም! ክቡር ሚኒስትሩ በጣም ተናደው ከሾፌራቸው ጋር እያወሩ ነው] ሰውዬ ለመሆኑ ጤነኛ ነህ? ክቡር ሚኒስትር ያጋጠመኝን እኮ ስላላወቁ ነው፡፡ ሁለት ቀን ሙሉ ስልክህን አጥፍተህ? በእነዚህ ሁለት ቀናት የደረሰብኝን መከራ ስለማያውቁ እኮ ነው? የላኩህ ቦታ ብጥብጥ አለ እንዴ? ብጥብጥ እንኳን አልነበረም ክቡር ሚኒስትር፡፡ ታዲያ ምን ሆነህ ነው ልትገኝ ያልቻልከው? የላኩኝን መልዕክት ለማድረስ ስንት መስዋዕት ስከፍል ነበር፡፡ የምን መስዋዕትነት ነው የምታወራው? ክቡር ሚኒስትር የሰጡኝ ሥራ ከፍተኛ መስዋዕት የሚያስከፍል ነበር፡፡ እህቴ የምትበላው ስለተቸገረች ለእሷ ጤፍ አድርስ አይደል እንዴ የተባልከው? እሱማ ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ ታዲያ ይኼን መሥራት ካልቻልክ ምኑን ሾፌር ሆንክ? ክቡር ሚኒስትር ሥራው እንዲህ ቀላል አይደለም እኮ? ምን ታካብዳለህ ሴትዮዋ በረሃብ ትሙት? ኧረ ክቡር ሚኒስትር ማንም ኢትዮጵያዊ በረሃብ መሞት የለበትም፡፡ ስማ ይቺ ሴትዮ ብትሞት ግን አንተ እንደገደልካት ማወቅ አለብህ፡፡ የተባለውን አልሰሙም እንዴ ክቡር ሚኒስትር? ምን ተባለ? መግደል መሸነፍ ነው ተብሏል፣ ስለዚህ እኔ መሸነፍ አልፈልግም፡፡ የፖለቲካ ዲስኩርህን እዚያው፡፡ ክቡር ሚኒስትር እኔማ የሰጡኝ ሥራ በቴክኖሎጂ ሳይቀር ታግዤ ለመሥራት አስቤያለሁ፡፡ ምንድነው የምታወራው?
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News