Blog Archives

በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል (በውብሸት ታዬ)

-ሆቴሎችና ባንኮች ተዘግተዋል -የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል -ተቃውሞው አራተኛ ቀኑን ይዟል ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ የ’መንጃ’ ብሔረሰብ አባል በአንድ ከፊቾ(የከፋ ብሔረሰብ አባል) ላይ ግድያ ፈጽሟል በሚል መነሻ በተቀሰቀሰ ግጭትና የበቀል እንቅስቃሴ በርካታ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በሰው አካል ላይም ጉዳት መድረሱን በቦታው የተገኘው ባልደረባችን ዘግቧል። የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከሳምንት በፊት የተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል በየኪ ወረዳ ቴፒ ከተማ በመገኘት በከተማው አዳራሽ የማሕበረሰቡን ተወካዮች ያነጋገሩ ሲሆን፤ በውይይቱ ወቅት የተወሰኑ አካላት ተደራጅተው ወደአዳራሹ በመሄድና እየደረሰብን ነው ያሉትን ጥቃት በተቃውሞ በሚገልጹበት ወቅት የተጠቀሙባቸው ቃላት የአከባቢውን ቀደምት ማሕበረሰቦች ክብር የሚነካ በመሆኑ ለችግሩ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል። የአሁኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴም ይህን ሆን ተብሎ የተደረገ ግጭት ቀስቃሽ መፈክር ሲያሰሙ የነበሩ ወገኖች ለፍርድ ይቅረቡልን የሚል መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ስብሰባው በዞኑ ዋና ከተማ በማሻ መደረግ ሲኖርበት በቴፒ መደረጉ የራሱ መልዕክት አለው የሚሉት ነዋሪዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል። በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ለችግሩ መፍትሔ ለማፈላለግ በሚል ተቃውሞው ከተቀሰቀሰባቸው ሶስት ወረዳዎች አንዷ ወደሆነችው የአንድራቻ ወረዳ ከተማ ጌጫ ከተለያዩ የማሕበረሰብ አባላት የተውጣጡ የሽምግልና ቡድን አባላት ሄደው እንደነበር ከቡድኑ አባላት አንዱ የገለጹልን ቢሆንም ይህ ዘገባ እስከሚጠናቀርበት ጊዜ ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን በሃዘኔታ ገልጸዋል። ከክስተቱ ጀርባ አሁን እየታየ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ የሚፈልጉ አካላት ግፊት አለበት ብለው እንደሚያምኑም ያላቸውን ግምት አስቀምጠዋል። መንገድ በመዘጋቱም የትራንስፖርት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News