Blog Archives

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የክልሉፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል የስራ ሂደት መሪ ኢንስፔክተር መሃመድ አህመድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ሁለት ቀን በፊት ከጉባ ወደ አሶሳ በሚመጣ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ዉስጥ በሁለት የልብስ ሻንጣ የተሞላ 5 መቶ የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ህብረተሰቡ በሰጠዉ ጥቆማ በሆሞሻ የፍተሻ ኬላ ላይ ጥይቶቹ ከአዘዋዋሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከባለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ከ37 በላይ የሚሆኑ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ መሃመድ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለዉ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ ሪፖርተር፡ ያለለት ወንድዬ (አሶሳ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook