የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ ጀመረ

የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ ጀመረ ።
እሁድ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመከስከስ አደጋ ያጋጠመውንና ለ157 ሰዎች ሕልፈት ምክንያት የሆነውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የአደጋ መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል።

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ በ ICAO Anex-13 መሰረት የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ አዋቅሮ ስራ ጀምሯል።

በዛሬው እለትም የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ሂደቱ ከሚስሳተፉ አባላት ውስጥ የNational transport safety board of America የምርመራ ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል ።
( ትራንስፖርት ሚኒስቴር )


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE