ከተከሰከሰው አይሮፕላን የሚገኙ አስከሬኖችን ለመለየት ቀናት ይወስዳሉ ተባለ

ከተከሰከሰው አይሮፕላን የሚገኙ አስከሬኖችን ለመለየት ቀናት ይወስዳሉ ተባለ

ከተከሰከሰው አይሮፕላን የሚገኙ አስከሬኖችን ለመለየት ቢያንስ አንድ አምስት ቀናት የሟቾች ቤተሰቦች መጠበቅ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ገለፁ።

Image result for Ethiopia crash bodies will take days to release

የሌሎችን መታወቂያ ለመለየት እጅግ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል ፤ ቢሆንም አስከሬን መቀበል ለመጀመር ቢያንስ አምስት ቀናትን መጠበቅ ያስፈልጋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ አቶ አስራት ባሻው ለአዲስ አበባ ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቁት አስከሬንን የመለቀቁ ሂደት ቢያንስ አምስት ቀናት ይወስዳል።ቤተሰቦች እንዲያውቁ ይደረጋሉ። ብለዋል።

በተከሰተው ጉዳት እና በቀጣይ የእሳት አደጋ ምክንያት የተወሰኑ ቅሪቶችን ለመለየት ሳምንቶች ወይም ወሮች ሊፈጅ ይችላል እና በጥርስ ህጋዊ መዛግብት ወይም ዲ ኤን ኤ በኩል ሊከናወን ይችላል፣ አንድ የኢንዱስትሪ ኤክስፐርት ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ምክንያቱም ተሳፋሪዎች ከ 30 በላይ ሀገሮች የመጡ በመሆናቸው እና ኢትዮጵያ የፎረንዚክ (ሕጋዊ የሕክምና ምርመራ) ስፔሻሊስት አቅም እምብዛም ስለማይታይ ሂደቱ ውስብስብ ይሆናል።

የ27 ዓመቱ የኬንያ ነጋዴ ነደርዲን መሐመድ ቤተሰቦቹ ሁለት ወንድማቸውን እና እናቱን ሁለቱን ለመቅበር መቼ እንደሚችሉ እንደማያውቁ ተናግረዋል።እኛ ሙስሊም ነን እና የሞተብንን ሰው ወዲያውኑ መቅበር አለብን። በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት አካል ማግኘት አልቻልንም በማለት ናይሮቢ ውስጥ ለሮተርስ ገልፀዋል። በዚያው ቀን አንድ ወንድምና እናቱን ማጣቱና ሰውነታቸውን ሳይቀበር መኖሩ በጣም ያምማል።ተናግሯል።( ትርጉም ምንሊክ ሳልሳዊ)

Source (Reuters)- https://af.reuters.com/article/topNews/idAFKBN1QT13L-OZATP


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE