ለ92 ሺህ 313 መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

በአገር አቀፍ ደረጃ በአንደኛ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 92 ሺህ 313 መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው፡፡

ስለፈተናው ሁኔታ ዛሬ ማብራሪያ የሰጡት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር ሙያ ብቃት አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክተር ወይዘሮ ካሳነሽ አለሙ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በሚሰጠው ፈተና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 58 ሺ 881 እንዲሁ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 33ሺ 432 በአጠቃላይ ለ92 ሺ 313 መምህራን፣ርዕሳነ ፣መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች ይፈተናሉ፡፡

ፈተናው መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም በሁሉም ክልሎች በ380 መፈተኛ ጣቢያ እንደሚሰጥ የጠቀሱት ወይዘሮ ካሳነሽ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካል ፈተናው በተያዘለት መረሃ ግብር መሰረት እንዲካሄድ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

(ኢፕድ)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE