6.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

6.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ።:በሞያሌ እና ጅግጅጋ የመቆጣጠሪያ ጣቢዎች በድምሩ 6,933,000 ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በቁጥጥር ዋለ።

No photo description available.

በሞያሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ ዕቃ ብዛቱ 4465 የሆነ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ መለዋወጫዎች እና 160 ኪ.ግ የሚመዝኑ ጫማዎች የሚገኝበት ሲሆን ግምታዊ ዋጋው 6,333,000 ብር ነው።

በተመሳሳይ ቀን ወደ ጅግጅጋ በመግባት ላይ እያለ የተያዘው የኮንትሮባንድ ዕቃ300 ሺህ ብር የተገመተ ሲሆን መድሃኒት፣ ኤሌክትሮኒክስና የተለያዩ አልባሳት ይገኝበታል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥራቸው 37408 አአ፣ ኮድ3-63611 እና 29817 ኦሮ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዙ ዘሪሁን ጌታቸው ከተባለ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር መዋላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE