ጎግል በመረጃ መፈለጊያ የፊት ገፁ ላይ ጥቁር ሪባን በማስቀመጥ የአውሮፕላን አደጋው ሰለባዎችን በማሰብ ላይ ይገኛል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥር አንድ የሆነው የመፈለጊያ ድረገፅ ጎግል/google.com/ እለቱን በትናንቱ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን እያሰበ ነው።

በቀን 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ጊዜ የሚጎበኘው ድረገፁ በመረጃ መፈለጊያ የፊት ገፁ ላይ ጥቁር ሪባን በማስቀመጥ የአደጋው ሰለባዎችን በማሰብ ላይ ይገኛል።

ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን አደጋ 157 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በአደጋውም ዓለም የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ ላይ ይገኛል።

በሀገር ውስጥም ዛሬ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ውሏል።

Image may contain: text


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE