በአዲስ አበባ ህዝባዊ ውይይት የታሰሩ ተለቀቁ

ትናንትና በአዲስ አበባ ባልደራስ አካባቢ ተደርጎ የነበረውን ሕዝባው ውይይት ተከትሎ ቢያንስ ሃያ ሰዎች ታስረው እንደነበር ነገር ግን አሁን መለቀቃቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል ።
የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ ወደየቤታቸው የሚያመሩ አንዳንድ ወጣቶች በተለይ ፒያሳ አካባቢ ወዳሉ የንግድ ተቋማት የመግባት ፍላጎት ስላሳዩ ፖሊስ ኅብረተሰቡን ከጉዳት ለመከላከል ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲሁም ወጣቶቹ ራሳቸውንም ከጥፋት ለመከላከል ሲል ከሃያ እስከ ሰላሳ የሚሆኑትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል ብለዋል ።

ኮሚሽነር ጄኔራሉ እንዳሉት አንድ ሺህ ሰዎች ይሳተፉበታል በሚል ፈቃድ ያገኘው ስብሰባ ላይ ስምንት ሺህ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ስብሰባው ግን በሰላም ተጠናቅቋል።

ይሁንና የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ ወደየቤታቸው የሚያመሩ አንዳንድ ወጣቶች በተለይ ፒያሳ አካባቢ ወዳሉ የንግድ ተቋማት የመግባት ፍላጎት ስላሳዩ ፖሊስ ኅብረተሰቡን ከጉዳት ለመከላከል ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት

እንዲሁም ወጣቶቹ ራሳቸውንም ከጥፋት ለመከላከል ሲል ከሃያ እስከ ሰላሳ የሚሆኑትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል ብለዋል።

አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ጭፈራ እያሰሙ ወደየቤታቸው መግባታቸው ታውቋል።

በህዝባዊ ውይይቱ ጋዜጠኛ የመብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ንግግረ ካደረጉ ሰዎች መካከል ነበር።

Image may contain: 3 people, people sitting and outdoor

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE