ከተከሰከሰው አይሮፕላን የተረፈው ዕድለኛው ግሪካዊዉ አንቶኒስ

ዕድለኛው ግሪካዊዉ አንቶኒስ እንደገለፀው

ምንጭ፡- ቻናል ኒውስ ኤስያ

ምንጭ፡- ቻናል ኒውስ ኤስያ

የበረራ ቁጥር 302 ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የሚበረውን አውሮፕላን ለመያዝ እየተጣደፍኩ ነው
ሻንጣዎቼ በዝተው በተመኘሁት ፍጥነት መጓዝ አልቻልኩም ማንም ሰው ሊረዳኝ ፍላጎት አላሳዩኝም ያለኝ አማራጭ በግሌ መውተርተር ነበር

Image may contain: one or more people and outdoor
የቱንም ያህል ተጣድፌ ብጓዝም በሰአቱ መድረስ አልተሳካልኝም በእርግጥ ሁለት ደቂቃውዎችን ብቻ ነበር የዘገየሁት
በቦታው ስደርስ መግቢያው እየተዘጋ ነበር የመጨረሻው ተሳፋሪ ሲገባ እያየሁት ነበር
ድምፄን ከፍ አድርጌ እባካችሁን አስገቡኝ ድካም ተሰምቶኝ በፍጥነት መጋዝ ሳልችል ነው የዘገየሁት በማለት መማፀን ጀመርኩ
ነገርግን ልመናዬን ሊሰሙኝ አልቻሉም
እጅጉን አዘንኩ
ሻንጣዎቼን ጭኜ ቢሆን ከ10 – 15 ደቂቃ ይጠብቁኝ ነበር በማለት አስቀድሜ ሻንጣዬን ባለመጫኔ ተቆጨሁ
በዕድሌ ክፉኛ በማዘን
ቀጣዩን አውሮፕላን ለመያዝ ወሰንኩኝ

ከደቂቃዎች በኃላ አውሮፕላኑ መከስከሱን ሰማሁ

No photo description available.

ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመሄድ ለስድስት ደቂቃ ብቻ በአየር ላይ ቆይቶ የተከሰከሰውና ለ149 መንገደኞችና 8 የበረራ ቡድኑ አባላት ሕልፈት ምክንያት የሆነው አውሮፕላን 150ኛ ተሳፋሪውን አምልጦት ነበር፡፡

‹‹ትረፍ ያለው›› ግሪካዊ መንገደኛ ለ2 ደቂቃ ዘግይቶ በመድረሱ ነበር አውሮፕላኑ ያመለጠው፡፡

አንቶኒስ ማቭሮፖሎስ የሚባለው ግሪካዊ ‹‹በጣም ተበሳጭቼ ነበር፤ በሰዓቱ ለመድረስ አልቻልኩም፤ ያገዘኝም አልነበረም›› ብሎ በፌስቡክ ገጹ የአውሮፕላን ትኬቱን ፎቶ ጨምሮ ለጥፏል፡፡

ያመለጠው አውሮፕላን የሆነውን ሲያውቅ ደግሞ የሕይወት ዘመኑ ወርቃማ ዕድል እንደሆነለት ተናግሯል፡፡

ምንጭ፡- ቻናል ኒውስ ኤስያ – https://www.channelnewsasia.com/news/world/greek-man-saved-from-ethiopian-airlines-et302-crash-being-late-11330576


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE