የኮንትሮባንዲስቶች ዋና አለቃ የጅቡቲው ጄኔራል ከድርጊቱ እንዲታቀብ አፋሮች ጠየቁ

በኣፋር ክልል እየተከሰተ ያለውና ኮንትሮባንድን ተገን አድርጎ የሚነሱ ግጭቶችና ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር በሚደረጉ አለመግባባቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ የኢትዮ ጅቡቲን ድንበር እያመሰው መሆኑን የክልሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ ።

ይህ የኮንትሮባንድ ቡድን የሚመራውና ዋና አለቃው የጅቡቲው ወታደራዊ ጄኔራል መሀመድ ጃማእ ነው። የኣፋር ክልል ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ኮንትሮባንዲስቱ አሸባሪ በአፍንጫችን ሥር ከምትገኝ ትንሽየ አገር ጁቡቲ ነው የሚኖረው።መሀመድ ጃማዕ የኢሳ ተወላጅ ነው። በኢትዮ ጁቡቲ የኮንትሮባንዲስቶች ዋና አለቃ በመሆን በትካሻው ላይ በደረደረው የጦር አዛዥነት ማዕረግ ተጠቅሞ የጁቡቲ ጦር ሐይል ዩኒፎርሙን አስወልቆ አርብቶ አደር በማስመስል የአፋር ህዝብ እያስጨፈጨፈ ይገኛል ይላሉ።

ለኮንትሮባንድ ንግዱ ይመቸው ዘንድ አከባቢውን የጦርነት ቀጠና ያስመሰለው መሀመድ ጃማዕ የኢሳ ተወላጅ ነው። በኢትዮ ጁቡቲ የኮንትሮባንዲስቶች ዋና አለቃ በመሆን በትካሻው ላይ በደረደረው የጦር አዛዥነት ማዕረግ ተጠቅሞ የጁቡቲ ጦር ሐይል ዩኒፎርሙን አስወልቆ አርብቶ አደር በማስመስል የአፋር ህዝብ እያስጨፈጨፈ ይገኛል። የጃማዕ ተግባር የተለመደ ነው። ለኮንትሮባንድ ንግዱ ሲል ምንም የማያውቀውን የኢሳ ሕዝብ እያስታጠቀ የእሳት ማገዶ በማድረግ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህ አንባገነን በአስቸኳይ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማድረግ መቻል አለበት።ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

Allo Yayo Abu Hisham (ኣፋር ክልል)

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE