አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ስድስት ኪሎ አካባቢ ባለቤቱን በጥይት ገደለ

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ስድስት ኪሎ አካባቢ ባለቤቱን በጥይት ገደለ

አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የስራ ባልደረባውና ባለቤቱ የሆነችውን የፖሊስ አባል ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት መግደሉ ተሰማ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል የሆነችውን የትዳር አጋሩን ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ መግደሉን አረጋግጠዋል።

መንስኤው ገና በመጣራት ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈፀመው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት መሆኑም ታውቋል።