ለማበድ እንኳን አገር ያስፈልጋል፤ በአገር ጉዳይ ምሁራንም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ገለልተኛ መሆን አይችሉም – መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ

… 16 ዓመት ሙሉ ትምህርት ላይ ቆይቶ ጭንቅላቱ ምንም ያልተዘራበት ሆኖ ይገኛል። ምሁራን ገለልተኛ መሆን የለባቸውም፤ ማንም ከአገር ጉዳይ ገለልተኛ ሊሆን አይችልም። አገር ሲኖር ነው ሁሉም ነገር የሚሆነው። አገር ከሌለ ማንም ሊኖር አይችልም።

ለማበድ እንኳን አገር ያስፈልጋል፤ በአገር ጉዳይ ምሁራንም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ገለልተኛ መሆን አይችሉም። በአገር ጉዳይ ላይ ማንም ነው መሥራት ያለበት፤ የአስተሳሰብ ቀረጻ ላይ መሰራት አለበት። አንድ ኢትዮጵያዊ አሜሪካ ውስጥ ቢያብድ ማደንዘዣ ተወግቶ ቦሌ ይጣላል። አንድ ሰው ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ማለት ይችላል፤ ‹‹ኢትዮጵያ የለችም›› ማለት ግን አይችልም። እግዚአብሔር የለም ቢል የሚመጣውን ራሱ ይቀበላል፤ ኢትዮጵያ የለችም ካለ ግን ሀገሩን ለቆ ኬንያ መግባት አለበት።
ከየካቲት 23 አዲስ ዘመን ቅዳሜ ዕትም ላይ የተወሰደ

ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=6023#