የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቋሚነት በአዲስ አበባ ብቻ እንዲካሄድ ተወሰነ።

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በዓመት አንድ ጊዜ በቋሚነት በአዲስ አበባ ብቻ እንዲካሄድ ተወሰነ። 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 3 እና 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ህብረቱ እያካሄደ ባለው ሪፎርም መሰረት የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በዓመት ስንት ጊዜ እና የት ይካሄድ በሚለው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚሁ መሰረት በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሪፎርም መሰረት የህብረቱ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ወስኗል።

ከሪፎሙ በፊት የመሪዎች ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ በየስድስት ወራት ልዩነት በአዲስ አበባ እና በዙር በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ከተሞች ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

በውሳኔው መሰረት ቀጣዩ 33ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ጥር 21 እና 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።.

የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ መውጣት ያበረከተችውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና አገራችን በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የዲፕሎማሲ ተሰሚነት ያገናዘበ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ያሰጠበቀ ነው።

MoFA


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE