ውንብድና በሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ 33ኛ አባይ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ።

ወታደራዊ መለዮ እየለበሱ ዝርፊያ እና ውንብድና በሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ተገለጸ
ወታደራዊ መለዮ እየለበሱ ዝርፊያ እና ውንብድና በሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ 33ኛ አባይ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ።

ክፍለ ጦሩ በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስተካከል ከሕዝቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የ33ኛ አባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ዓለሙ አየነ ሠላምን ለማስፈን በሁለቱም ዞኖች ከ37 ሺህ በላይ ሠዎችን ማወያየታቸውን ተናግረዋል። እርቅና መግባባት ላይም ተደርሷል ነው ያሉት።

በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ታውቋል።

እስካሁንም በቡድንና በግል ሆነው በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጀነራል ዓለሙ ገልፀዋል።

ምንጭ አብመድ