በማእከላዊ ጎንደር ጥፋት ያደረሰው ኃይል በሁለት ከፍተኛ ቡድኖች የተደራጀ፤ የታጠቀና ስምሪት የተሰጠው ኃይል ነው፡፡ ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌ

” በማእከላዊ ጎንደር ጥፋት ያደረሰው ኃይል በሁለት ከፍተኛ ቡድኖች የተደራጀ፤ የታጠቀና ስምሪት የተሰጠው ኃይል ነው፡፡ “

የአማራ ክልላዊ መንግስት የደህንነትና ሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ

(ኢ.ፕ.ድ)

• ከሰሞኑ በማእከላዊ ጎንደር ጥፋት ያደረሰው ኃይል በሁለት ከፍተኛ ቡድኖች የተደራጀ፤ የታጠቀና ስምሪት የተሰጠው ኃይል ነው፡፡ አንደኛው ቡድን ቤቶችን የሚያቃጥል ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የመጀመሪያው ቡድን እንቅፋት ቢያጋጥመው ሊከላከል በሚችልበት ሁኔታ የተዘጋጀ ነበር፡፡

• የተቀናጀውና የተደራጀው ኃይል በሁለት አቅጣጫ ነው የመጣው፡፡ አንደኛው ቡድን ከ200 በላይ ፤ሁለተኛው ከ70 እስከ 80 ሰው የሚገመት የታጠቀና የተደራጀ ሃይል እንደነበረው ይገመታል፡፡

• ብሬንና ድሽቃ የተባሉ የቡድን ከባድ መሳሪያዎችን ተጠቅሟል፡፡ ይሄን መጠቀም የሚችለው የሰለጠነና ፕሮፌሽናል የሆነ ኃይል ብቻ ነው፡፡

• በድንገት በሰነዘሩት ጥቃት ከ30 በላይ ሰው ሕይወት አልፏል፡፡ ከ300 በላይ የአርሶ አደር ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡

• ጥቃቱን የፈጸመው ከሌላ ቦታ በተለይ ከምእራባዊ ጎንደር አቅጣጫ ተጭኖ በተለየ መንገድ ሰርጎ የሚገባ ኃይል ነው፡፡

• በከሚሴ አካባቢ ከጎንደሩ ጋር በተመሳሳይ ወቅትና በተቀናጀ መንገድ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ የሰው ሕይወት አልፏል፡፡ አውራ ጎዳናዎች ለመዝጋት ተሞክሯል፡፡

• ከፍተኛውን አደጋ የመከላከል ስራ የሰራው መከላከያ ሰራዊት ነው፡፡ የተዘጉትን መንገዶች በሙሉ አስከፍቷል፡፡

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE