የኤርትራ ወደቦችን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወደቦችን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን መልሶ ለመገንባት የ20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሁለቱን ሀገራት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን የህብረቱ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኔቨን ሚምካ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በማጠናከርና ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን የሚታወስ ነው፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE