ኢትዮጵያ ባለፉት 2 ዓመታት ከ 70 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢን አጥታለች

በኢትዮጵያ 40 በመቶ ያህሉ ነጋዴ በግብር ስርአት ውስጥ ያልገባ እና ግብር የማይከፍል መሆኑ ተነገረ፡፡በኢትዮጵያ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩትን የሚያካትት መሆኒ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ሪፎርም ንቅናቄ እንዲያካሂድ ምክንያት እንደሆነው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ 40 በመቶ ያህሉ ነጋዴ በግብር ስርአት ውስጥ ያልገባ እና ግብር የማይከፍል መሆኑ ተነገረ፡፡በኢትዮጵያ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩትን የሚያካትት መሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ሪፎርም ንቅናቄ እንዲያካሂድ ምክንያት እንደሆነው ታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳለው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የመስሪ ቤቱን ሰራተኞች ዳግም ከማዋቀር ጀምሮ 34 ልዩ ልዩ ህጎችን የማስተካከል እና ህግን የማስከበር ስራ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጧል፡፡

በተለይ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ጠንከር ያለ ቁጥጥር እየተካሄደ ነው ያለው ሚኒስቴሩ ያም ሆኖ ግን በሃገሪቱ የሚገኙ 94 የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን በተደራጀ አኳኋን የሚልፉ የውጭ ሃገር ገንዘቦች ዝውውር ላይ ያተኮረ የውጭ ኮንትሮባንድ ጭማሪ አሳይቷል ብሏል በመግለጫው፡፡ በተለይ ሃገሪቱን ኢኮኖሚዋን በማሽመድመድ ሚና የነበራቸው አንዳንድ ህጎች እንዲሻሻሉ እየተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከቀረጥ ነጻ ተጠቃሚ የሚያደርገው ህግ መታገዱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በሃገሪቱ በተንሰራፋው ህገውጥ የንግድ ስርአትና የግብር አሰባሰብ ችግር ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታትማግኘት የነበረባትን ከ 70 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተነግሯል፡፡ ሚኒስቴሩ እግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የጀመረው የታክስ ሪፎርም ዘመቻ በሁሉም ክልሎች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡