የሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ የመከላከያ ሰራዊት የሚያደርገው የተኩስ ልምምድ ተቃውሞ ገጠመው።

የሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ

Image may contain: sky, outdoor and nature

እንደሚታወቀው የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ለሚያከብረው ዓመታዊ የመከላከያ ቀን በዓል በሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ሊያከብር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ከፓርክ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ድርጊቱን ለማስቆም በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም መስቆም እንዳልቻለ ከመከላከያ ሚኒስቴር በተሰጠ ምላሽ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ተቋሙ እንከመጨረሻው ሰዓት የሚችለውን እንደሚያደርክ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
በፓርኩ ውስጥ የተፈጠረውን የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳትም በዛሬው ዕለት የመከላከያ ኃይል በፓርኩ ክፍል ውስጥ የሚያካሂደውን የልምምድና የተኩስ ዝግጅት በአካል በቦታው በመገኘት በፓርኩ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማየት ተችሏል፡፡

ዝግጅቱም ሙሉ ለሙሉ በፓርኩ ውስጥ ይባስ ብሎም የዱር እንስሳቱ በደረቅ ወቅት በሚጠለሉበት አካባቢ መሆኑ ችግሩ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ስነ-ስርዓቱም በታንክ፤ በመድፍ፤ በጄት እንዲሁም በኢሊኮፕተር ተኩስና ትሪት የታጀበ መሆኑ፤ ለተኩስ አውድማ እና ኢላማ የተለየው ቦታ በአሰቦት ተራራ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኝ ኮረብታማና ተራራማ ቦታ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይህም ለተኩስ ትሪት የተለየው ቦታ የግሬቪ ዜብራ፤የሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ የተለያዩ አዕዋፋት ሰጎንንም ጨምሮ ዋና መገኛና መኖሪያ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Image may contain: sky, tree, outdoor and nature

አስር ኪ.ሜ ስኩዬር አካባቢ የሚሸፍነው የልምምድ ዝግጅቱ በቁጥር ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ ታንኮች፤ በርከታ ያለ ቁጥር ያላቸው መድፎችን የያዘ ነው፡፡

ይህ ደግሞ ከተሳቢ ነፍሳት ጀምሮ እስከ ትልልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት ህይወት እስከማጥፋት ድረስ ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጥር ለማዬት ተችሏል፡፡
በቦታው በመገኘት እንዳገኘነው መረጃም የመከላከያ የበላይ ኃላፊዎች የችግሩን አሳሳቢነት እና ጉዳቱን ገልፀንላቸው ወደ ፓርኩ ክፍል እንደገቡ አምነው የተቆፈረው የፓርኩ ክፍል፤ በንቅስቃሴ ወቅት የተቆፋፈሩት የፓርኩ ሜዳማ አካባቢዎች፤ የሳር ክፍሎች ወደ ምድረ በዳነት መቀየርን ፤ በልምምድ ጊዜ ዱር እንስሳቱ ሲረበሹ እንዳዩ እና ችግር እንዳስከተለ ገልፀው በቀጣይም በተኩስ ጊዜ በሚፈጠረው ከፍተኛ ድምፅ እና በተኩሱ ትሪት ወቅት የዱር እንስሳቱ እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

በሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ የመከላከያ ኃልይል ላለፉት ቀናት ብሎም ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በፓርኩ ውስጥ የተለያዩ ትሪቶችን ሲያደርግ የቆየ መሆኑና በሚቀጥለው እሁድ ከፍተኛ ድምፅ የሚያስተጋቡ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም የተኩስ ትሪት የሚያሳይ በመሆኑ በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ነው፡፡

ስለሆነም ይህ የተፈጥሮ ሀብቱን ህልውና የሚገዳደርና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ድርጊቱን የሚያከናውነው የመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ላስከተለው የተፈጥሮ ሀብት ጥፋትና ውድመት ተገቢውን ካሳ የሚከፍልበትን መንገድ መፈጠር እንዳለበት ይህ ካልሆነም ለሚደርሰው የተፈጥሮ ሀብት ጉዳት የመከላኪያ ሚኒስቴር ሙሉ ኃላፊነቱን መውሰድ እንዳለበት ባላስልጣን መስሪያ ቤቱ ሊያሳስብ ይወዳል፡፡

Via Ethiopian Wildlife Conservation Authority


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE