ኢ/ር ታከለ ኡማ የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው ተመረጡ

ኢ/ር ታከለ ኡማ የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው ተመረጡ

ኢ/ር ታከለ ኡማ የመረጡት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ በሆነው African Renaissance and Diaspora Network የተባለ ተቋም ነው፡፡

የተቋሙ ፕረዝዳንት ዶ/ር ጂብሪል ዲያሎ ኢ/ር ታከለ ኡማ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየሰሩት ባለው የልማትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች እና የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰሩ ባለው ስራ የአፍርካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለምአቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ( Global Alliance of Mayors and Leaders; East African Chair) አድርጎ መምረጡን አሳውቋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይነትም ሃገሪቷ የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፍ እና በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያሉ ከፍተኛ የት/ት ተቋማትን በማጣመር ወጣት የከተማዋ ነዋሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚንቀሳቀስም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፡- ከንቲባ ፅህፈት ቤት


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE