አብን በሀገር አቀፍ ደረጃ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግኝቷል።

አብን የፖለቲካ አድማሱ በክልል ብቻ የታጠረ አለመሆኑን አስታወቀ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግኝቷል።

Image may contain: 2 people, people smiling, people sitting

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥር 28/2011 ዓ.ም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።

የተመዘገበውም ሀገራዊ ሆኖ ነው። የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት የአብን የፖለቲካ አድማስ በክልል ብቻ የታጠረ ባለመሆኑ ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው።

ይህም ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ያስችላል ነው ያሉት አቶ ክርስቲያን። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ አማራዎችን ለመድረስ እንዲቻል ማድረግም ሌላውም ምክንያት ሆኖ ቀርቧል።

No photo description available.

አብን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመተባበር ለሀገር አስተዋፅኦ በማድረግ ለአማራ ሕዝብ ከሀገር የሚገባውን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚሰራም አብራርተዋል።

ከፓርቲ ይልቅ ንቅናቄ ሆኖ የተመዘገበውም ከፖለቲካ ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ በባህልና በሌሎችም የአማራን ሕዝብ ክብር ለማስመለስ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ነው ብሎዋል አቶ ክርስቲያን።

ንቅናቄው ሰኔ 3/2010 ዓ.ም ነው የተመሠረተው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE