አምቦ ዩኒቨርሲቲ በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስም የጥናት ማእከል ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስም የጥናት ማእከል ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ

የጥናት ማእከሉ መቋቋምም እንደ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ያሉ ምሁራንን ለማፍራት አላማ ያደረገ መሆኑንም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ ተናግረዋል።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ እየተቋቋመ ያለው የጥናት ማእከልም በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የስነ ፅሁፍ ስራዎች ላይ ምርምር ማድረግ እና እንደ ሎሬት ፀጋዬ ያሉ ምሁራንን ለማፍራት የሚያስችል ነው ብለዋል ዶክተር ታደሰ።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን አምቦ አካባቢ ቦዳ ተብላ በምትታውቅ ስፍራ ነው በ1928 ዓ.ም የተወለዱት።

በአምቦ ሀገረ ሕይወት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአሀር ውስጥ ትምህርታችውን ከተከታተሉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ትምህራቸውን አጠናቀቁ።

በ1952 ወደ እንግሊዟ ለንደን ከተማ በማቅናት በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴዝ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ከ1954 እስከ 1964 የብሔራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት ያገለገሉ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የቴአትር ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።

የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያሉ የስነ ጽሁፍ ፍቅር ያደረባቸው ሎሬት ፀጋዬ ህይወታቸው እስካለፈበት 1998 ዓ.ም ድረስ በርካታ ግጥሞችን እና የስነ ፅሁፍ ስራዎችን፣ የቴአትር ሥራዎችን እና ዘፈኖችን አበርክተዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE