የሰኔ 16ቱ ቦንብ ጥቃት ተባባሪ እና የጠ/ሚ አብይን ስልክ በመጥለፍ መረጃ ሲያቀብል የነበረ ባለስልጣን መለቀቁ እያነጋገረ ነው።

ኢሣያስ ዳኘዉ: የሰኔ 16ቱ ቦንብ ጥቃት ተባባሪ እና የጠ/ሚ አብይን ስልክ በመጥለፍ መረጃ ሲያቀብል የነበረ ግለሰብ በዋስ ተለቀቀ!  አቃቤ ህግ ምን እየሰራ ነው?? ( ስዩም ተሾመ)

እንዴ… ቆይ ግን መርማሪ ፖሊሶች እና አቃቢ ህግ የሚሰሩት ለማን ነው? እንደ ቀድሞው ለህወሓት ነው? ወይስ በህጉ መሠረት ነው? ተጠርጣሪን ወንጀለኛ አልክ” ቅብርጥስ ይባላል ብለን ዝም አልን እንጂ አቶ ኢሣያስ ዳኘዉ ምን ሲሰራ እና ከማን ጋር ሲዶልት እንደነበረ እናውቃለን እኮ?! ከዚህ በኋላ ግን ያረረበት_ያማስል! በተጨባጭ የማውቀውን መረጃ እዚህ አወጣዋለሁ፡፡ አቶ ኢሣያስ ዳኘዉ ከፈለገ “በሃሰት ስሜን ጠፍቷል” ብሎ ይክሰሰኝ፡፡ እንደውም ሥራውን በማስረጃ አስደግፌ ለማጋለጥ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡ አቶ ኢሳያስ ከፈፀማቸው የወንጀል ተግባራት ውስጥ የሚከተሉትን በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ ይቻላል፦

አንደኛ፦ ሰኔ 16/2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የቦንብ_ፍንዳታ በደረሰበት ቅፅበት በአከባቢው የስልክ ግንኙነት እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገው በወቅቱ የኢትዮቴሌኮም የኦፕሬሽን ክፍል ሃላፊ የነበረው አቶ ኢሣያስ ዳኘዉ ነው፡፡ በእንዲህ ያለ የሽብር ወንጀል የተሳተፈ ግለሰብ ነው እንግዲህ በዋስ የተለቀቀው!!!

ሁለተኛ፦ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የቢሮ ስልክ ተጠልፎ እንደነበር ከወራት በፊት በይፋ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የሀገሪቱን ጠ/ሚኒስትር የስልክ መስመር እንዲጠለፍ በማድረግ መቀሌ ለመሸገው የማፊያ ቡድን መረጃ ሲያቀብል የነበረው አሁንም አቶ ኢሣያስ ዳኘዉ ነው፡፡ እንዲህ ያለ በሀገር_ክህደት ሊከሰስ የሚገባ ግለሰብ ነው በዋስ የተለቀቀው!! #MinilikSalsawi