“የአባገዳዎችን ጥሪ ዉድቅ በማድረግ የማገኘው ነፃነት ይቅርብኝ።” – ኤልያስ ጋቤላ ማን ነው?

“የአባገዳዎችን ጥሪ ዉድቅ በማድረግ የማገኘው ነፃነት ይቅርብኝ።”
.
ኤልያስ ጋቤላ ማን ነው?
.
ጓድ ኤልያስ የትግል አጋሮቹ በቅጽል ስሙ አብረሃም ሊንከን ብለው የሚጠሩት ሲሆን በሁለቱም የጉጂ ዞኖች የሚንቀሳቀሰው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ጦር መሪ ነው። ይህ ጀግና ሰው የተወለደው በጉጂ ዞን ሀርቃሎ ከተማ ሲሆን ወደ ትግል ከመግባቱ በፊት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ሙያ በመጀሪያ ድግሪ የተመረቀ እና በመምህርነት ሙያ ያገለግል ነበር።


በሁለቱ የጉጂ ዞኖች የኦነግ ጦር መሥራች እና ከዚህ በፊት የደቡብ ዞን ኦነግ ተብሎ የሚጠራውን የአነግ ጦርን ከ 4 አመት በፊት መልሶ ያቋቋመ ታጋይም ነው። የትግል አጋሮቹ ኤልያስን የኦሮሞ አንድነት አባት እና የውጊያ ሳይንስን ጠንቅቆ የሚያውቅ ጠንካራ መሪ ይሉታል።
.
ይህ ቆራጥ ታጋይ የአባጋዳዎችን ጥሪ በመቀበል ታህሳስ 5, 2011 ዓ.ም በተለያዬ ደረጃ የሚገኙ የጦር መሪዎችን እና ወታደሮችን ይዞ ወደ ህዝብ በመቀላቀሉ የአካባቢው ህዝብ በክብር እና በፍቅር የጀግና አቀባበል አድርገውለታል። ከአባገዳዎችም ጋር ተገናኝቶ እንደተናገረው ከ150 አመት በላይ የኦሮሞ ህዝብን የትግል ታሪክን ብንመለከት የኦሮሞ ህዝብ በአሁኑ ግዜ የተሻለ እድል አግኝቷል። ችግሮችም አሉ ነገር ግን ይህ ግዜ ከአንድ እናት እና አባት የተወለዱ የኦሮሞ ልጆች እርስ በእርስ መዋጋት ያለባቸው ግዜ አይደለም:: ስለመዋጋት እንኳን አንዳች ቃል መናገር የለባቸውም ብሏል። ስለዚህም ከአሁን በኋላ በኦሮሞ ልጆች መሀከል የሚካሄደው ጦርነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት። ይህን አቋሙን ተግባራዊ ለማድረግ የተቀሩት ጓዶቹም የአባጋዳዎችን ጥሪ ተቀብለው የሚገቡበት ሁኔታ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
.
ታገይ ኤልየስ እንደገለፀው ኦሮሞ ኦሮሞን ገድሎ የሚገኝ ድል አሳዛኝ፣ሞት እና ታሪክን ማበላሸት ወይም ማጥቆር ነው። በመሆኑም ጫካ ያሉት በሠላም ገብተው በስልጣን ላይ ያለው አካልም ወደ እኛ በመቅረብ ኦሮሞን ማስከበር አለብን ይላል። የኦሮሞን እና የመላው ኢትዮጵያውያንን ጥቅም በማስጠበቅ ህዝባችን የስልጣን ባለቤት በሚሆንበት ሁኔታ ላይ መሥራት ነው እንጂ ጦርነት አያስፈልግም ሲልም አክሏል። እንደ እርሱ አገላለጽ የኦሮሞን ልጆችን ሞት ከማስቆም የሚበልጥ ትግል የለም። እኛ ኦሮሞዎች ከተደማመጥን እና የአባገዳዎችን ምክር ካዳመጥን የማንፈታው ችግር የለም ብሏል። በመጨረሻም ለኦሮሞ ህዝብ ድል ማለት መደማመጥ ነው በማለት ንግግሩን ቋጭቷል።
.
© Nagessa Oddo Dube