የአርቲስት ሄለን በድሉና የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ቤተሰብ

የአርቲስት ሄለን በድሉና የጄኔራል ክንፈ ቤተሰብ

የሜቴኩ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እህት አልማዝ ትባላለች። ታላቅ እህቱ ነች። ቀብራራዋ አልሚ አሁንም በአዲስ አበባ ትኖራለች። ሚሊዬነር ልጅ አላት ማሙሽ ጎይቶም ይባላል። ሚሊዬነሩ ማሙሽ የአርቲስት ሄለን በድሉ ባለቤት ነው። በስማቸው ምህፃረ ቃል የተሰየመው ሄለንና ማሙሽ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች መሸጫ መደብር (H&M furniture) ባለቤት ነው።

ቱጃሩ ማሙሽ መሸት ሲል በየጊዜው በፌስታል ገንዘብ ይዞ ሰገባ ይስተዋላል። እናቱ ቤት እየኖረም አሁንም በራሱ ቤት ከሄለን ጋር እየኖረው በፌስታል ብር መሸከሙን አጠናክሮ ቀጥሏል። ምናልባትም የቤተሰባቸው የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ በመታገዱ በመኖሪያ ቤቱ ጊዜያዊ ባንክ ሳይከፍት አይቀርም። ለማሙሽ ሚሊዬነር መሆን ቢሊዬነሩ ክንፈ ታላቅ ባለውለታው ነው። የሜቴኩ ባላባት አባ ስጠው ክንፈ ለእህቱ ልጅ ለመቋቋሚያ ትሆነው ዘንድ 100 ሚሊዬን ብር የሰጠው ሲሆን፤ ማሙሽም ፈርኒቸር ቤቱን በመክፈት የአጎቱን ገንዘብ ጥቅም ላይ አውሎታል። ማሙሽ የስራ ሰው ነው። ቀደምም ብሎም ወደ ኖርዌይ መሄድ ለሚፈልጉ ቪዛ በማመቻቸት ገንዘብ ያገኝ ነበር። ኖርዌይ ሃገር የሚኖረው ሌላው ወንድሙ የአውሮፓውን ማሙሽ የሃገር ውስጡን ጉዳይ ያስጨርሱ ነበር። እድሜ ለአጎት ክንፈ!

በጄኔራል ክንፈ የክስ መዝገብ ላይ የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ እግድ ከተጣለባቸው እነ ሻሼ ምስራቅ የሚባሉትን ስም ዝርዝር ጋር የነማሙሽ ስም አብሮ ባለመጠቀሱ ምናልባት ማሙሽና እናቱ ከክሱ ጋር ያልተገናኙ ይሆናሉ። ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ምብራት ዳኘው፣ አብርሃም ዳኘው፣ ኢሳያስ ዳኘው፣ አከቦም ክንፈ ዳኘው፣ ማርዳ ክንፈ ዳኘውና ሌሎችም የባንክ ሂሳባቸው ላይ እግድ እንደተጣለባቸው የሚታወስ ነው።

የአርቲስት ሄለን በድሉና የማሙሽ ኤች ኤንድ ኤም ፈርኒቸር አዲስ አበባ 22 ማዞሪያ ከርብቃ ህንፃ ( አክሱም ሆቴል) ጀርባ 50 ሜትር ገባ ብሎ ጦቢያ ጠጅ ቤት ፊት ለፊት ወይም ከሌክስ ፕላዛ ህንፃ አለፍ ብሎ ባለው መታጠፊያ ኬር ኢትዮጵያ ህንፃ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን፤ በተለይ ዘመናዊ ሶፋዎችን በማቅረብ ይታወቃል።

ለዝርዝሩ ጴጥሮስ አሸናፊ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE