አንድ ባለስልጣን ለልማት ስራ የተሰበሰበ 2 ሚሊየን 70 ሺ ብር ከባንክ በማዉጣት ተሰወሩ

በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ህብረተሰብ ተሳትፎ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለም ገ/ሚካኤል ከህብረተሰቡ ለልማት ስራ የተሰበሰበ 2 ሚሊየን 70 ሺ ብር ከባንክ በማዉጣት መሰወሩ ተገለፀ ።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።

ህብረተሰቡም አስፈላጊውን መረጃ እንዲስጥ እየጠየቅን የምርመራ ዉጤቱን እየተከታተልን የምናሳውቅ ይሆናል ሲል የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መግለፁን የካ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በማኅበራዊ ገጹ አስነብቧል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE