ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት ከዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፌስቡክ ገፅ ተመልክተናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን፣ ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፤ የሚመደቡባቸውን አገራት ፖሊሲ የመገንዘብና በአገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብት የማስጠበቅ ሚና እንዳላቸው መናገራቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

ውይይቱ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውስጥ የተደረጉትን ለውጦች ለመገምገም ያቀደ ነውም ተብሏል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE