ከቡሌ ቦራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታና የመንግሥት ምላሽ

DW AMHARIC  – በቡሌ ሆራ ዩኒቭርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንት ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲውን ለቅቀው ወደየ ትውልድ አካባቢያቸው ተመልሰዋል፡፡

Image result for ከቡሌ ቦራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታና የመንግሥት ምላሽ
ከአንድ ወር በፊት ወደ ባሕር ዳር የመጡት የአማራ ክልል ተወላጆችም በጊዚያዊነት በባህር ዳር ሰታዲዮም ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ የኢኖቬሽንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ጥር 1 እና 2 /2011 ዓ.ም ተማሪዎቹ ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመለሱ በብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ታዲያ ይህንን ጥሪ ተቀብለው ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እንደማይመለሱ ነው በባህር ዳር ሰታዲየም በጊዚያዊነት ተጠልለው ከሚገኙት መካከል ያነጋገርኳቸው የቡሌ ሆራ ተማሪዎች የሚናገሩት። በተለይም ሴቶች ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ተግባሮች እንደተፈፀሙባቸው ነው የሚናገሩት ። በዚህም ምክንያት ወደ ቡሌ ሆራ እንደጋና መመለስ አይታሰብም ያ የሚሆን ከሆነ ሌላ ቅጣት መሆኑን በምሬት ተናግረዋል።

ሀገር የምንኖርበት እንጂ እየሞትን የምንገነባው አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ መንግስት ቀርቦ ችግራቸውን ከስር መሰረቱ እንዲያውቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ መንግስት በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሰቲዎች አንዲመድባቸው ነው ሁሉም «DW» ያነጋገራቸው ተማሪዎች የተናገሩት፡፡

ስለጉዳዩ እንዲነግሩኝ የትምህርት ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ዳይረክተሯን በስልክ ለማነጋገር ብሞክርም ፈቃደኛነታቸውን ከገለፁልኝ በኋላ ቀጠሮ በያዙልኝ ሰዓት ብደውልና ስልካቸው ቢጠራም አንስተው ለማነጋገር አልፈቀዱም፡፡ የፌደራል መንግስት የኢኖቬሽንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በአጭር የእንግሊዝኛ ጽሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ተማሪዎቹ በሚፈልጓቸው ዩኒቭርሲቲዎች መመደብ የሚሆን አይደለም፣ የተለያዩ መስፈርቶችን ተመልክቶ ምደባውን በመላ አገሪቱ በሚገኙዩ ኒቨርስቲዎች የሚመድበው የትምህርት ሚኒስቴር ነው፣ ቡሌሆራ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ከዩኒቨርሲቲው ወጥተው የነበሩ ተማሪዎችን ከጥር 2/2011 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና እየመዘገበ ነው፡፡ ሁሉም ተማሪዎች አንደገና ተመዝግበው ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ የሚል አምነት አለን፣ ያን አለማድረግ ግን የራስ ውሳኔ ነው” ቡሌ ሆራ ዩኒቨረሲቲ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ዉስጥ ይገኛል፡፡