የኃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ከዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

የኃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ከዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

የኃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ከትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ-መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በመቀሌ ከተማ ተወያይተዋል፡፡

የሰላም ሀሳብ በመያዝ ወደ ትግራይ ክልል ያቀኑት የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን በፅፈት ቤታቸው ተገኝተው አነጋግረዋል፡፡

የኃይማኖት መሪዎቹ በኢትዮጵያ ከእንግዲህ ማንም ሲፈናቀል፣ ህፃናት ሲጎዱና መንገዶች ሲዘጉ ማየት እንደማይፈልጉ ለክልሉ ርእሰ-መስተዳደር ገልጸውላቸዋል፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን በበኩላቸው የትግራይ ህዝብና መንግስት ዋነኛ አጀንዳ ከድህነትና ኋላቀርነት በመውጣት የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አሁን በአገሪቱ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልል መንግስታት እና የፖለቲካ መሪዎች በጋራ ለሰላም መስራት እንዳለባቸውም የሀይማኖት አባቶቹ ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE