የታህሳስ ወር የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

የታህሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የዋጋ ግሽበቱ በምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶች 9 ነጥብ 1 እንዲሁም ምግብ ነክ ባልሆኑ እቃዎችና አገልግሎቶች 11 ነጥብ 4 ሆኖ ተመዝግቧል።

ኢኮኖሚያቸውን በሚገባ መቆጣጠር በሚችሉ ያደጉ ሃገራት የዋጋ ግሽበት በአብዛኛው ከ2 እስከ 5 በመቶ እንደሆነና ይህም ተመራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ያስቀምጣሉ።

ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ የተስተዋለው የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ቢሆንም ከ5 አመታት በፊት ከነበረበት ከፍተኛ መጠን ያለው ግሽበት አንፃር ኢኮኖሚውን በከፋ ሁኔታ የሚጎዳ አለመሆኑን ነው የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ለገሰ የገለፁት።

ኤጀንሲው የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ መነሻ ዓመትም ከ2004 ወደ 2009 እንዲሆን አድርጓል።

የመነሻ አመቱን መቀየር ያስፈለገው አሁን ያለውን የገበያ ዋጋና የምርት ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑም ነው የተመለከተው ሲል የዘገበው ኤፍ ቢሲ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE