በኦሮሞ እና ሶማሌ ገሪ እና ጃርሶ ጎሳዎች መካከል ተፈጥሮ ለቆየው ግጭት የሰላም መፍትሄ ለማበጀት ከስምምነት ተደረሰ

በኦሮሞ እና ሶማሌ ገሪ እና ጃርሶ ጎሳዎች መካከል ተፈጥሮ ለቆየው ግጭት የሰላም መፍትሄ ለማበጀት ከስምምነት መደረሱን የአካባቢው ሸምጋዮች አመለከቱ። የሁለቱ ጎሳዎች ተወላጆች በጋራ ባሏቸው እነሱ ሔር በሚሉት ባህላዊ ሕግ መሠረት ለመፍትሄው በ30 ቀናት ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ መወሰኑንም ሽማግሌዎቹ ለDW ገልጸዋል።

የግጭቱ መንስኤ ለ27 ዓመት የተዘራ የፖለቲካ ሥራ ነው ያሉት እርቅ ለማውረድ ሲሰሩ የቆዩት የሁለቱ ወንድማማች ጎሳዎች ሽማግሌዎች በተገኘው አዎንታዊ ውጤት መደሰታቸውም ተነግሯል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE