ሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሀገር እንዲመጡ ጥሪ ተደረገ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ አድረገ።

ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ሊደረግ መሆኑን  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደሮቹ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሀገር እንዲመጡ ነው ጥሪው የተደረገላቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ከ60 በላይ አገሮች የሚገኙ የኢፌዴሪ አምባሳደሮች በመጪው ሰኞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ተገለጸ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው ሳምንታዊ የወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮችና አምባሳደሮች የአገሪቱ ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሚዳብርበት ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ይወያያሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሻሻያ፣ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ያከናወነችው ተግባራትና የቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫ ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ታውቋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE