የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለዜጎች ደህንነት ዋስትና መሆን ሲገባው ለዜጎች ስጋት መሆን የለበትም፡፡

በምእራብ ጎንደር ዞን በገንዳውሃ ከተማና በኮኪት ቀበሌ በንፁሃን አማራዎች በደረሰው የህይወት መጥፋት የሰሜን ጎንደር አስተዳደርና ህዝብ ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶታል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለዜጎች ደህንነት ዋስትና መሆን ሲገባው ለዜጎች ስጋት መሆን የለበትም፡፡ ሌላ ተልእኮ ካልኖረ በስተቀር ህዝብ ተወያይቶ መፍትሄ እስኪሰጥ ድረስ እንዴት መታገስ ያቅታል?

የሱር ኮንስትራክሽን በአካባቢው ህዝብ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን በተደጋጋሚ ነዋሪዎቹ ሲናገሩ መቆየታቸው እየታወቀና መኪናዎቹ ተፈትሸው ይለፉ ማለት ለክልላችን መንግስትና ለህዝቡ ደህንነት ዋሰትና መሆኑ ታውቆ ሊበረታታ ይገባው ነበር እንጅ እንዴት ይተኮስበታል? እነዴትስ ይገደላል?

ድርጊቱ በጣም ስህተትና አጸያፊ ስለሆነ አዴፓ የሚመራው የክልሉና የፌድራሉ መንግስት በጋራ በመሆን አጥፊዎችን በአስቸኳይ አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖቻችን በሰሜን ጎንደር ዞን ህዝብና መንግስት ስም መጽናናትን እንመኛለን፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት
ጥር02/2011 ዓ.ም


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE