እኛ የዚህች ሀገር መስራች ነን፤ከዚህ በኋላ በኦጋዴን ምንም አይነት ውጊያ አይኖርም፡፡- የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ወቅታዊ አቋሙን፣ ይቀርቡበት የነበሩትን ክሶችና ቀጣይ መንገዱን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግሯል

-ላለፉት 27 ዓመታት በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምበት ነበር፡፡ እንደ ሰው የህዝብን መብት ማክበር ካልቻልክ ሴቶችን ከደፈርክ ከገደልካቸው ካጠፋሀቸው ለምንድነው የሀገሪቱ አካል የምንሆነው ?

-በሶማሌ ክልል የተገኘው ነዳጅ የሚወጣ ከሆነ የግድ በክልላዊ መንግስቱና በፌዴራል መንግስቱ መካከል ድርድር መኖር አለበት፤ እኩል ድርሻም መኖር አለበት፤

– ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ምህዳሩን ከፍቶታል፡፡ አቋሙ እጅግ በጣም ቀና ነው፤ እጅግ በጣም እናደንቀዋለን፤

– ከዚህ በኋላ በኦጋዴን ምንም አይነት ውጊያ አይኖርም፡፡

– እኛ የዚህች ሀገር መስራች ነን፤

-የኦብነግ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አድሚራል መሀመድ ኡመር ኡስማን የቀድሞዋ ሶማሊያ የባህር ሃይል አዛዥ ነበሩ፤

– ኦብነግ ሶማሌ ክልልን በመገንጠል ታላቋ ሶማሊያ እንድትመሰረት ፍላጎት አለው ይባላል፤ የድርጅቱ ግብ ይህ ይሆን?

-እአአ በ2007 እኤአ በኦጋዴን ነዳጅ ፍለጋ ስራ ላይ በነበሩ ቻይናውያንና ኢትዮጵያውያን ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በርካቶች ሞተዋል፤ በወቅቱም ጥቃቱን ኦብነግ መፈጸሙን በይፋዊ ድረ ገጹ አስታውቋል ተብሎ ነበር፤ በእርግጥ ጥቃቱን የፈጸመው ኦብነግ ነው?

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ኦብነግ በድረ ገጹ ኢሕአዴግ እምነት የሚጣልበት ድርጅት አይደለም፡፡ መለወጡን የሚያሣዩ ተግባራዊ እርምጃዎች ወስዶ ማየት እንፈልጋልን ብሎ ነበር፡፡ ኦብነግ ለውጡን እንዴት ይገመግመዋል?

-የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ጸሃፊና መስራች አቶ አብዱልራህማን መሀዲ ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ አላቸው። የዋና ጸሀፊውን መልስ በነገው የሀሙስ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይመልከቱ፤


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE