በብዙዎች የማይታወቀው የ560 ኪሎ ሜትር የበረሃ ላይ የሩጫ ውድድር

ዘ ስፒድ ፕሮጀክት፤ ከሎስ አንጀለስ እስከ ላስ ቬጋስ የሚደረግ፤ እስካሁን ቅጣት ያልተላለፈበት፤ ስፖንሰር የሌለው 563 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የሩጭ ውድድር ነው። ድረ-ገፅ የለውም። ‘እዚህ ይመዝገቡ’ የሚል አማራጭም አልያዘም። ሕግ የለውም። በዚህ ነው መንገዱ የሚል ጥቆማ አይገኝም። ተመልካች ማግኘት ፈፅሞ አይታሰብም። ውድድሩ አንድ ሳምንት እስኪቀረው ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት አዳጋች ነው።…