ጎንደር ገንደውሀ ላይ አምስት ሰወች መገደላቸውን ተከትሎ ተቃውሞና ውጥረት ነግሷል

ገንዳውሃ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ጉዳይ እጅግ አሳዛኝ ነው። የሱር መኪኖች ከገንዳ ውሃ አልፈው ወደ ኮኪት አቅንተው ነበር። የሱር መኪኖች ካለፉ በኋላ የመከላከያ ኦራሎች ወደ ገንዳውሃ ገብተው ሩምታ መተኮስ ጀመሩ። በዚህ ሂደት ህፃናት ተገድለዋል። ደግንጠው የጮሁ ሴቶችም “ምን ሆናችሁ?” ተብለው ተተኩሶባቸው ቆስለዋል።

የገንዳ ውሃ ከተማ ሕዝብ መኪና ለማቆም እንዳልጣረ የአካባቢው ምንጮች አረጋግጠዋል። የሱር መኪኖች ካለፉ በኋላ ነው ገንዳውሃ ላይ ጭፍጨፋ የተፈፀመው።

ይህ ሆን ተብሎ በሰበብ የተደረገ ጭፍጨፋ ነው። እስካሁን ከ28 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ከ9 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE