ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችው በከንቲባው ጠባቂ የታገተችው ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተሰማ

Imageፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተሰማ

ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያክል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ መመለሷን አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡

በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ አዲስ ማለዳ በቦታው ካሉ ምንጯቿ ያገኘችው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ ጸጋ ነጻ ብትወጣም እገታውን የፈጸመው የፖሊስ አባል አለመያዙ ታውቋል፡፡

ግንቦት 15/2015 የግል ተበዳይ ፀጋ በላቸው፤ ከሥራ ወጥታ ወደ ግል ጉዳይ በምታመራበት ወቅት በተለምዶው አሮጌው መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጠለፋው እንደተፈፀመባት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመነሐሪያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአዲስ ማለዳ መግለጹ ይታወሳል።

ጸጋ መታገቷ ከተሰማ በኋላ ፖሊስ ከፍተኛ ክትትል ሲዲርግ መቆየቱን የገለጸ ሲሆን፤ እሳካሁን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የጠጠረጠሩ ስምንት ሰውች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ  አዲስ ማለዳ