ጠ/ሚ አብይ የድሬዳዋ ጉዟቸውን የሰረዙት በፀጥታ ችግር ምክንያት ነው ተባለ።

Ethio News flash Exclusive News

ከሳምንታት በፊት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በድሬዳዋ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመመረቅ አስበው በመጨረሻ ሰአት ጉዟቸውን የሰረዙበት ምክንያት ከፀጥታ ችግር ጋር የተያያዘ መሆኑን የከተማዋ ሁለት ሀላፊዎች ለኢትዮ ኒውስፍላሽ በተለይ ገልፀዋል።

አንዱ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሀላፊ እንዳመለከተው ወደ ፕሮጀክቶቹ ከሚወስዱት መንገዶች አንዱ የመልካ መንገድ ዙርያ የጦር መሳርያ በብዛት በወቅቱ እንደተገኘ ሲገልፅ ሁለተኛው ሀላፊ ደግሞ ሌሎች የመንገድ አማራጮችን ጠ/ሚሩ ተጠቅመው መሄድ ቢችሉም የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ስላልነበር ሙሉ ለሙሉ ጉዞው ተሰርዟል ብለዋል። ነገር ግን ሁለቱም ሀላፊዎች ጠ/ሚሩ በወቅቱ ኢላማ ውስጥ እንደነበሩ ተጠይቀው በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።

የጠ/ሚር ቢሮን በጉዳዩ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ ጠይቀን እስካሁን መልስ እየጠበቅን መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE