በጋዜጠኛ ደምስ ስም ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው

በጋዜጠኛ ደምስ ስም ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው

በአርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴ አማካኝነት የጋዜጠኛ ደምስ በለጠን ቤተሰቦች ሊያጽናኑ ከኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር፣ ከሞረሽ እና ከአብን የተውጣጡ ልዑክ ቡድኖች ዶክተር ዳኛቸው ፣አቶ ማሙሸት አማረ፣ ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ በለጠ ሞላ፣ ጋሻው መርሻ ( አብን) ሃኒባል ፣በቀለ እና የሞረሽ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዲቱ በመሆን ወደ ጋዜጠኛው ቤት አቅንተው ነበር፡፡ በነበራቸው የማጽናኛ ፕሮግራም ላይ በአቶ ደምስ ስም ፋውንዴሽን ሊቋቋም መሆኑ የሞረሽ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዘውዲቱ ይፋ አድርገዋል፡፡ የደምስን ስም ህያው ለማድረግ እና የጀመረውን የትግል ጉዞ ዳር ለማድረስ የጉዞው አባላት ቃል ገብተዋል፡፡ ጋዜጠኛ እና መምህር የጀመራቸውን ስራዎች ለማስጨረስ እና ህልሙን ለማሳካት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የደምስ ስራዎች ለመቀጠል እና ዳር ለማድረስ የአማራን ትግል ለማገዝ በሚደረጉት ሂደቶች አርበኛ እና ጋዜጠኛ መንግስቱ (የአማራ ድምጽ ሪፖርተር ) ላይ ከፍተኛ ሃላፊነት እንደተጣለበት እና እሱም በሙሉ ፍቃደኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ገልጹዋል፡፡

የጋዜጠኛ ደምስ ወላጅ እናትም ‹በናንተ ኮርቻለሁ ልጄ አልሞተም ለጀመረው ሁሉ እንደምትጨርሱለት አምናለሁ እግዜር የጀመራችሁትን ያስጨርሳችሁ ሲሉ› ምርቃት እና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የአማራ ድምጽ ራዲዮን አድማስ ለማስፋፋት እና የአማራ ሚዲያን ለማቋቋማ ከሰላሳ አመት በኋላ ኢትዮጵያ ቢመጣም በድንገት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
የአማራ ድምጽ ራዲዮ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE