በሐረር ከተማ የቡድን ዝርፊያን ጨምሮ በየቀኑ የሚስተዋሉ ህገወጥ ድርጊቶች ነዋሪዎችን አስግቷል

በሐረር ከተማ የቡድን ዝርፊያን ጨምሮ በየቀኑ የሚስተዋሉ ህገወጥ ድርጊቶች መበራከታቸው ህብረተሰቡን በስጋት እንዲኖር አድርጎታል ሲሉ የከተማይቱ ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ። የከተማይቱን ጸጥታ የማስከበር ድክመት እንዳለ የሚቀበለው የሐረሪ ክልል የፍትህ ቢሮ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በሐረር ከተማ የቡድን ዝርፊያን ጨምሮ በየቀኑ የሚስተዋሉ ህግ እና ስርዓትን ያልተከተሉ ድርጊቶች መበራከታቸው ህብረተሰቡን በስጋት እንዲኖር አድርጎታል ሲሉ የከተማይቱ ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ። ነዋሪዎቹ የኮንደሚንየም ቤታቸው በህገወጦች ተሰብሮ እንተወሰደባቸው እና ከሚኖሩበት ቤት የቀበሌ ቤት በግዴታ እንዲለቅቁ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ህግ እና ጸጥታን የማስከበር ኃላፊነት ያለባቸው አካላትም ስራቸውን በአግባቡ አለመስራታቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል። ችግሩ እንዳለ የሚቀበለው የሐረሪ ክልል የፍትህ ቢሮ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE